07 February 2010

ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስደተኛ ተማሪዎች ኬንያ ዩኒቨርሲቲዎች እየገቡ ነው

47 ሰዎች የተገደሉበትና 3 ሺህ ተማሪዎች የታሠሩበትን የአምናውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመፅ ውጤት ሸሽተው ኬንያ የተሰደዱ ተማሪዎች መካከል 200 የሚሆኑትን በኬንያ ዩኒቨርስቲዎች ለማስተማር አንድ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተዘገበ።

በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩትና የቦይንጉ ስፔስ ሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ለዚህ በጎ ተግባር የተነሳሱት ለሥራ ጉዳይ ወደ ኬንያ ተጉዘው በነበረበት ወቅት የስደተኛ ተማሪዎቹን ያሉበትን ሁኔታ የመመልከትዕድሉ ስላጋጠማቸው መሆኑን በአሜሪካ ሀገር የሚታተመው "ዘኢትዮጵያን"ጋዜጣ ዘግቧል።

በሥራና በሙያ አጋጣሚ ኢንጅነር ቅጣው ኬንያ መሄድ ነበረባቸው። በአጋጣሚ ወጣት፣ ትምህርት ፈላጊ ግን ስደተኛ ወገኖቻቸውን በተመለከቱበት ወቅት አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው አሰላሰሉ። በዚሁ መሠረት ተማሪዎቹ ያቋረጡትን ትምህርት እንዲቀጥሉ ለማድረግ ተነሳሱ። ሆኖም ግን ሁሉም ነገር ቀላል አልሆነላቸውም። የኬንያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቹ ስደተኛ መሆናቸው ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ እንደ ኬንያውያን ታይተው በዚያ ልክ እንዲከፍሉ ጥያቄ አቀረቡ። ጥያቄያቸው ተቀባይነት አገኘ። ይህም ሆኖ ቀሪው ሥራ ከባድ ነበር።

ኢንጂነሩ "እኔም የማገኛትን ለነዚህ ወጣት ተማሪዎች ማዋል እንዳለብኝ ተገነዘብኩ። እነዚህ ወጣቶች ቢማሩ አገር ይገነባሉ። አገሬ ሁሌም እንዲህ ሆና አትቀርም በማለት ያለኝን እያካፈልኩ " ነው ይላሉ።

"200 ኢትዮጵያዊያን እንኳንስ በወጪ በአገር ውስጥ ማስተማር ይከብዳል። ወገን ከተባበረ ግን ሸክሙ አይከብድም" የሚሉት ኢንጂነር ቅጣው ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻቸውን በማስተባበር 38 ተማሪዎች ጆሞ ኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ አድርገዋል። በቀጣይነት 69 ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ለመግባት በሂደት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል። ቀሪዎቹ ተማሪዎች ደግሞ ሞይ እና ዴይስታር ዩኒቨርሲዎች ለመግባት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ እያሟሉ መሆናቸውን ኢንጂነሩ ለጋዜጣው ሪፖርተር ገልፀዋል።

"እንዳልኩህ 38 ዩኒቨርሲቲ የጀመሩ ተማሪዎች ቤት ተከራይተንላቸዋል። ቢያንስ አራት አራት ሆነው በጋራ እየሠሩ፣ እያበሰሉ እንዲኖሩ አድርገናል። ለኑሯቸውም ቢሆን ማሰብ ይኖርብናል።

በዚህ ላይ የትምህርት ቤት ክፍያው ቀላል አይደለም። የመላው ኢትዮጵያዊያን ድጋፍና ዕርዳታ በእጅጉ ያስፈልገናል።" ብለዋል ኢንጂነሩ።

እንደ ኢንጂነር ቅጣው ገለፃ ከሆነ 38ቱን ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለማስተማር በትንሹ 115 ሺህ ዶላር ያስፈልጋል ካሉ በኋላ በዕርዳታው መሳተፍ የሚፈልጉ በተለይ በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ወገኖቻችን መተባበር እንደሚችሉና ድጋፉ ከታክስ ነፃ ሊያስደርግ የሚችል መሆኑንም ተናግረዋል።

ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ በናሳ በቦይንግ እና በመስኩ ባሉ የቴክኖሎጂ የአቬዬሽንና የስፔስ ሲስተም ሳይንቲስትነት ከ32 ዓመት በላይ አገልግለዋል። በአሁኑ ሰዓት በቦይንግ ስፔስ ኤንድ ኮሚዩኒኬሽንስ ቡድን የኮማንድ ሲስተም ውስጥ እየሠሩ እንደሚገኙ ታውቋል።

ከዘፕሬስ ሐምሌ 24 ቀን 1994

Text generator

በናሳ በቦይንግ እና በመስኩ ባሉ የቴክኖሎጂ የአቬዬሽንና የስፔስ ሲስተም ሳይንቲስትነት ከ32 ዓመት በላይ አገልግለዋል። በአሁኑ ሰዓት በቦይንግ ስፔስ ኤንድ ኮሚዩኒኬሽንስ ቡድን የኮማንድ ሲስተም ውስጥ እየሠሩ እንደሚገኙ ታውቋል።

ከዘፕሬስ ሐምሌ 24 ቀን 1994

Text generator

No comments:

Post a Comment